የክልል ክለቦች ሻምፒዮናው ግማሽ ፍጻሜ ላይ ደርሷል!!

34

ወልድያ: ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በወልድያ ከተማ አስተናጋጅነት የቀጠለው የአማራ ክልል እግር ኳስ ክለቦች ውድድር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ተደርገዋል። አራት መርሐ ግብሮች በዕለቱ ሲደረጉ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የገቡ ክለቦች ታውቀዋል።

ትናንት በተከናወኑ ጨዋታዎች :-

ሙጃ ጎንጅ ደብረጥበብን 2 ለ 1 ፣ ቆቦ ከደሴ ከነማ ቢ በመደበኛ ሰዓት 2 አቻ አጠናቅቀው በተሰጠ መለያ ምት 4 ለ 3 ያሸነፈው ቆቦ ግማሽ ፍጻሜ ገብቷል።

በተመሳሳይ ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ከቁንዝላ ጋር ያለግብ ተለያይቶ በመለያ ምት ደብረ ታቦር 5 ለ 4 መርታት ሲችል ፣ ጣና ክፍለ ከተማ እና መካነ ኢየሱስ 2 አቻ ከተለያዩ በኋላ ጣና በመለያ ምት 5 ለ 4 በኾነ ውጤት አሸንፈዋል።

አሸናፊዎቹ ክለቦች ማክሰኞ የዋንጫና የደረጃ ተፋላሚ ቡድኖችን ለመለየት የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብራቸውን ያከናውናሉ።

⚽️ ጣና ክፍለ ከተማ ከሙጃ

⚽️ ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ከቆቦ ተጋጣሚ ክለቦች ናቸው።

ዘጋቢ:- አማኑኤል ጸጋዬ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋየ (ዶ.ር) በደቡብ ጎንደር ዞን ተገኝተው ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አሳረፉ።
Next articleበምርት ዘመኑ በአማራ ክልል 8 ሚሊዮን ኩንታል የሩዝ ምርት ለማግኘት እየተሠራ መኾኑን ግብርና ቢሮ ገለጸ።