
ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ወጅ ቀበሌ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ተካሄዷል። በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላው የሴቶች ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋየ ተገኝተው አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በችግኝ ተከላው ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚኒስቴር ዴኤታ መክዩ መሐመድ፣ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ኃይለማርያም ከፍያለው (ዶ.ር) እና ሌሎችም የፌደራል፣ የክልል እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች አሻራቸውን አሳርፈዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!