
ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የ2015/2016 ምርት ዘመን የሩዝ ክላስተር ዘር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦከምከም ወረዳ እየተካሄደ ነው። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የሩዝ ኩታ-ገጠም ዘሩን አስጀምረዋል።
ኩታ-ገጠሙ የሚገኘው በወረዳው ቡራ ቀበሌ ሲኾን በዚሁ ቀበሌ ብቻ 482 ሄክታር መሬት ሰብል ይሸፈናል ተብሏል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ አዲስ ተፈራ በዚህ ዓመት 50 ሺህ ሄክታር ሩዝ በኩታ-ገጠም ለማልማት እየተሠራ ነው ብለዋል። እስካሁን ድረስም 80 በመቶው መሬት በዘር ስለመሸፈኑ አስረድተዋል። በ2015/2016 የምርት ዘመን 2 ሚሊዮን ኩንታል ሩዝ ለማምረት መታቀዱንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!