ዶክተር አምባቸው መኮንን በደብረታቦር ከተማ ትምሕርት ቤት ተሰየመላቸው።

83

ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረታቦር ከተማ እና አካባቢው ተወልደው ለሀገራችው በርካታ ሥራ የሠሩ እና ወጣቱ ትውልድ እንዲማርባቸው በአርዓያነትም ፈለጋቸውን እንዲከተል በማሰብ ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ጉባኤውን ሲያካሂድ ተቋማትን በስማቸው ሰይሟል፣

በዚህም መሰረት፦

1ኛ) በድሮ ቀበሌ 06 በአሁኑ አፄ ገላውዴዎስ ቀበሌ የሚሠራው አዲስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዶክተር አምባቸው መኮንን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሆኖ እንዲሰየም፣

2ኛ ) ቀጭን መስክ 1ኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ወደ ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሆኖ እንዲሰም፣

3ኛ) የደብረታቦር ጤና ጣቢያ ወደ ክቡር ዶክተር ዓለማየሁ ስመኝ ጤና ጣቢያ ተብሎ እንዲሰየም ሲወሰን ባደረጉት በርካታ ሥራዎች በመነሳት እንደሆነና ከሀምሌ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ስያሜው ተግባራዊ እንዲሆን ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በተመሳሳይ መረጃ የደብረታቦር ከተማ ምክር ቤት በከተመው ለሚገኙ ጎዳናዎች ስያሜዎችን ሰጥቷል።

በሀገራችን የታሪክ አውድ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለነበራቸው እና ላበረከቱ አስተዋጽኦ ግለሰቦች ለመታሰቢያቸው የጎዳና ስያሜ ተሰጥቷል።

ምክር ቤቱ የጎዳና ስያሜዎችን ሲሰጥ ለሀገራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰበች ይገባቸዋል ብሎ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ባቀረበው ሰነድ እና እንዲፀድቅለት በጠየቀው መሰረት በሰፊው ከተወያዬ በኃላ እንደሚከተለው ውሳኔውን አስተላልፏል።

የጎዳናዎች ስያሜን በተመለከተ፡-

1ኛ)ፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ ቀበሌ 07 ከሚገኘው ከዋናው አስፓልት / ቄስ አበበ ቤት/ ተነስቶ ወደ ኢንዱስትሪው ሰፈር የሚወስደው ባለ አካፋይ መንገድ፣

2ኛ)ጄኔራል ነጋ ተገኜ ከእቴጌ ጣይቱ ኃውልት አደባባይ እስከ ደብረታቦር ጤና ጣቢያ ያለው አስፓልት መንገድ፣

3ኛ)ቢትወደድ አዳነ መኮነን ከአፄ ቴዎድሮስ ኃውልት አስከ እቴጌ ጣይቱ አደባባይ የሚወስደው አስፓልት መንገድ፣

4ኛ)ሻንበል አጥናፉ ገላው ቀበሌ 05 የሚገኘው ከዋናው አስፓልት ተነስቶ በመነሃሪያ ጀርባ እስከ ዋናው አስፓልት ድረስ ያለው ኮብል ስቶን መንገድ፣

5ኛ)ዶ/ር አለማየሁ ከበደ ከአፄ ቴዎድሮስ ኃውልት አስከ ማረሚያ ቤት ድረስ ያለው አስፓልት መንገድ፣

6ኛ)አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከአፄ ቴዎድሮስ ኃውልት አስከ ስላሴ ቤተክርስቲያን መንገድ (ከዚህ ቀድም የተሰየመ)

7ኛ)ዶ/ር ኦጋምቢክ ቀበሌ 06 ከሚገኘው ፋርጣ ወረዳ ጽ/ቤት አስከ ቀበሌ 06 ጽ/ቤት ድረስ ያለው ጎዳና፣

8ኛ)አቡነ መልከፀዲቅ ቀበሌ 01 የሚገኘውን ከአጅባር ሜዳ እስከ ልጅቱ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለው ኮብል ስቶን መንገድ፣

9ኛ)አለቃ ገብረሃና ቀበሌ 04 ከአራዳ ገብያ ከማህደረ ማርያም አስፓልት መንገድ አስከ ቀበሌ 04 ጽ/ቤት ዋናው አስፓልት ድረስ ያለው አስፓልት መንገድ፣

10ኛ)ጥቅምት 24 ጎዳና ከትራፊክ ላይት እስከ ሰኞ ገብያ ድረስ ያለው አስፓልት መንገድ፣

11ኛ)ሀምሌ 5 ጎዳና ሰኞ ገብያ ከሚወስደው አስፓልት መንገድ አንስቶ ወደ ታቦር 1ኛ ደረጃ የሚወስደው ኮብል ስቶን መንገድ፣

12ኛ)ቢትወደድ ገሰሰ ረታ ቀበሌ 06 ክልል ውስጥ ከቄስ አለማየሁ አስከ እቴጌ ጣይቱ ኃውልት አደባባይ ድረስ ያለው መንገድ፣

13ኛ)ሌ/ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ከትራፊክ ላይት አስከ እቴጌ ጣይቱ አደባባይ ያለው አስፓልት መንገድ፣

14ኛ)ራስ አሞራው ውብነህ ከእቴጌ ጣይቱ ኃውልት አደባባይ እስከ አዲሱ ዩኒቨርስቲ የሚወስደው መንገድ፣

15ኛ)ግራ አዝማች አድማሱ በላይ ከፈረንጁ ቤተክርስቲያን አንስቶ ወደ ሰኞ ገብያ የሚወስደው አዲስ የተሰራው መንገድ፣

16ኛ)አቡነ ኤልሳዕ ከቄስ አለማየሁ ቤት ተነስቶ ወደ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን የሚወስደው አዲስ የተሰራው መንገድ፣

17ኛ)ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ከፋርጣ ወረዳ ጽ/ቤት እስከ እቴጌ ጣይቱ አደባባይ ድረስ ያለው ኮብል ስቶን መንገድ፣

18ኛ) ቀኝ አዝማች አሻግሬ መራ ቀበሌ 02 ከሚገኘው ከድሮው ማዘጋጃ ቤት ኮብልስቶን መነሻ አድርጎ በአደባባዩ ጀርባየሚወስደውና ከዋናው አስፓልት የሚገናኘው ኮብልስቶን መንገድ፣

19ኛ)መምህር እንደስራቸው አግማሴ ቀበሌ 06 ከሚገኘው ዋነው አስፓልት ከደ/ጎ/ዞ/ከተማና መ/ል/መምሪያ ተነስቶ ወደ ሰላምኮ የሚወስደው ኮብል ስቶን መንገድ፣

20ኛ)ፀባቴ ገብረስላሴ ወንድም አገኝ ቀበሌ 07 የሚገኘው ወደ ቅድስት አርሴማ የሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ፣

21ኛ)ሰዓሊ አገኘሁ እንግዳየሁ ቀበሌ 08 ከዋናው አስፓልት አንስቶ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን የሚወስደው ኮብል መንገድ፣

22ኛ) ዶ/ር አዳሙ አንለይ ወደ ኢትዮጵያ ሆቴል ከሚወስደው የአስፓልት መንገድ እስከ ሙስሊም መስጊድ ድረስ ያለው መንገድ፣

23ኛ)ዶ/ር ሂሩት ካሳሁን ቀበሌ 01 ከሚገኘው ከፍትህ መምሪያ እስከ ፈረንጁ ቤተክርስቲያን እስከ አቡነ መልከ ፀዲቅ ድረስ ካለው ኮብል ስቶን መንገድ፣

24ኛ)ቀኝ አዝማች ምስጋናው አዱኛ DTM ሆቴል አንስቶ በህብረት ጀርባ የሚገኘው የኮብል ስቶን መንገድ፣

25ኛ)ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከሆስፒታሉ በፍትህ መምሪያ ወደሰኞ ገብያ የሚወስደው ኮብል ስቶን መንገድ፣

26ኛ)እቴጌ መነን ቀበሌ 03 የሚገኘው ወደ ስላሴ ቤተክርስቲያን ከሚወስደው የአርቲስት ማዲንጎ ጎዳን ከድሮው ቀበሌ 03 ጽ/ቤት አንስቶ ወደ ቀበሌ 03 የአንድ ማዕከል የሚወስደው ኮብል ስቶን መንገድ፣

27ኛ)ደራሲ ገሪማ ታፈረ ቀበሌ 01 ከትራፊክ ላይት አንስቶ ወደ ሰኞ ገብያ የሚወስደው ጥቅምት 24 ጎዳና አንስቶ ወደ ሰኞ ገብያ የሚወስደው ኮብል ስቶን መንገድ፣

28)አርቲስት ታማኝ በየነ ከፖሊስ ጽ/ቤት አንስቶ ወደ ጤና ጣቢያው አስፓልት ቁልቁል የሚወስደው ኮብል ስቶን መንገድ፣

29ኛ)”አለሜ” ከአጼ ቴዎድሮስ ኃውልት አንስቶ ቁልቁል አራዳ ገብያ የሚወስደው ኮብል ስቶን መንገድ፣

30ኛ)”ገልሞ” ከቴዎድሮስ አደባባይ /አበጀ ሆቴል/ ወደ ቀበሌ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት የሚወስደው ኮብል መንገድ፣

31ኛ)ጄኔራል ፈንታ በላይ ቀበሌ 03 ውስጥ ወደ ደ/ታቦር ኢየሱስ የሚወስደው የአርቲስት ማዲንጎ ጎዳና አንስቶ ወደ ታቦር ት/ቤት ቁልቁል የሚወስደው አዲስ የተሰራው ኮብል ስቶን መንገድ፣ እንዲኾን ተወስኗል።
የጎዳናዎች ስያሜ ከሃምሌ 01/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ምክር ቤቱ ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

መረጃው የደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዛሬ አዲሰ አበባ የሱዳንን ግጭት በድርድር ለመፍታት በኢጋድ የተወከሉ መሪዎች ይወያያሉ።
Next article“በአማራ ክልል ከደረጃ በታች ያሉ ትምህርት ቤቶችን ታሪክ ለማድረግ እየሠራን ነው” ማተብ ታፈረ (ዶ.ር)