
ከሚሴ: ሐምሌ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በዞኑና በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ያለመ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር በከሚሴ ከተማ አካሂዷል።
በውይይቱ የጸጥታ ኀይሉ እና ኅብረተሰቡ በጋራ በመኾን ባከናወኑት ተግባር አስተማማኝ ሰላም እየተፈጠረ መኾኑ ነው የተገለጸው።
በዞኑ ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት ሰላምን የሚያውኩ ችግሮች ተከስተው እንደነበር የሚገልጹት የውይይቱ ተሳታፊዎች፤ በተከናወኑ ተግባራት አሁን ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ተናግረዋል።
አሁን ላለው ሰላም የጸጥታ ኀይሉ እና የኅብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ እንደነበርም ጠቅሰዋል። የተገኘውን ሰላምም ለማስቀጠል በጋራ እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ በዞኑ ግጭቶችን ለማስቆምና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተከናወኑት ተግባራት ውጤታማ መኾናቸውን ገልጸዋል።
የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል በቀጣይም በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ነው ዋና አሥተዳዳሪው የተናገሩት። ለዚህም በቅንጅት ይሠራል ብለዋል።
በውይይቱ ላይ የዞን እና የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም በቀጣናው ያሉ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፓሊስ መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!