
ባሕር ዳር: ሐምሌ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች “ለማንነቴ እሮጣለሁ፤ ማንነቴም አማራ ነው” በሚል መሪ መልእክት የጎዳና ላይ ሩጫ አካሄዱ።
በሩጫውም ላይ የተሳተፉት ነዋሪዎቹ ላለፍት 30 ዓመታት በማንነታቸው ምክንያት ሲደርሳባቸው ከነበረው በደል፣ ግፍና ጭቆና በመላቀቃቸው እንዲሁም ተፈጥሮዓዊ ማንነታችን አማራ ነው፣ የነፃነት ማንነታችን ይከበር በማለት ደማቅ የጎዳና ላይ ሩጫ አካሂደዋል። መረጃው የአማራ ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ነው::
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!