የጣና ሞገዶቹ ባሕርዳር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

15

ባሕር ዳር: ሐምሌ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የጣና ሞገዶቹ ባሕርዳር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል።

የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ እና የከነማ እግር ኳስ ክለብ የበላይ ጠባቂ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ክለቡ ባሕርዳር ሲገባ ባደረጉት ደማቅ አቀባበል የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መላው የከተማችንና አካባቢው ማኅበረሰብ ፣ የክለቡ አመራርና ደጋፊዎች እንዲሁም የክለቡ ተጫዋቾችና አሠልጣኞች በነበራቸው የፀና ትግል ለከተማችን ድምቀት የኾነው ክለብ ለዚህ ስኬት በመድረሱ ደስታችን ወሰን የለውም ብለዋል።

ዶክተር ድረስ በቀጣይ ክለቡ የጀመረውን የስኬት ጉዞ በድል አጠናቅቆ ውጤታማ እንዲኾን የገንዘብና የሞራል ድጋፍ በመስጠት ትግላችንን ፍፁም ሰላማዊ በኾነ መንገድ ደግፈን ዋንጫውን የምናሸንፍበትን እድል ማስፋት ይጠበቅብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሥራ ዕድል ፈጠራ የኢትዮጵያ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም አፍሪካዊ ጉዳይ ነው መኾኑን ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
Next article«ለማንነቴ እሮጣለሁ፤ ማንነቴም አማራ ነው» የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች