15ኛው የአማራ ክልል ባህልና ኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል ሁለተኛ ቀን ውሎ በሙሉዓለም የባህል ማዕከል መካሄድ ጀምሯል።

54

ባሕር ዳር: ሐምሌ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የባህል ሙዚቃና ውዝዋዜ ውድድር በትላንትናው ዕለት የጎንደር ከተማ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ደብረ ማርቆስ ከተማ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ደሴ ከተማ፣ ምዕራብ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስደናቂ ዝግጅት አሳይተዋል።

ዛሬ ደግሞ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ወሎ፣ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ደብረ ታቦር እና ወልድያ ከተማ አስተዳደሮች ውብ ባህላዊ ሙዚቃና ውዝዋዜ በማቅረብ ፉክክሩን የሚቀላቀሉ ይሆናል።

ከሰዓት በአማራ ክልል ምክር ቤት በሚኖር መረሃ-ግብር ደግሞ ለባህልና ኪነ-ጥበብ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ሽልማትና እውቅና ይሰጣቸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ሐምሌ 10 በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ በመትከል ታሪክ እንዲሠራ ጥሪ አቀረቡ።
Next article“በክረምት ያለ ቤት”