“የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ለዓለም ለማስተዋወቅ በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ላይ በትብብር መስራት ይገባል” የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

50

ባሕር ዳር: ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ለዓለም ለማስተዋወቅ አረንጓዴ ዲፕሎማሲ ላይ በትብብር መሥራት እንደሚገባ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።

ለአየር ንብረት የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ ቀርጸው እየሰሩ ካሉ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ በቀዳሚነት እንደምትጠቀስ ገልጸዋል።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በዘርፉ ልማት ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው ያሉ ሥራዎችን በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም ኢትዮጵያ በደን ልማት፣ በአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና እንክብካቤ የተሳካ ስራ መስራቷን አንስተዋል።

በእርከን ሥራና የአፈር ለምነትን በመጠበቅ ከፍ ያለ ስም ማትረፏን ጠቅሰው በአረንጓዴ አሻራ ልማት የጀመረችው ጥረትም አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ለዓለም ለማስተዋወቅ በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ላይ በትብብር መስራት የሚገባ መሆኑንም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ከራስ አልፎ የአካባቢውን አገራት ተጠቃሚነትም ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ለቀጣናዊ የልማት ትስስር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በሁለተኛው ምእራፍ የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር 25 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል እቅድ ይዛ በመሥራት ላይ ትገኛለች።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበ2016 ዓ.ም የአማራ አንደኛ ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ታውቀዋል።
Next article“ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት ሩስያ ድጋፍ ታደርጋለች” በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር