
ወልድያ: ሀምሌ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል ክለቦች ሻምፒዮና በወልዲያ ከተማ መካሄዱን ሲቀጥል ውድድሩ ወደ ሩብ ፍጻሜ የገቡ ክለቦች ተለይተዋል።
የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎቹ ትናንት ሲጠናቀቁ 8ቱ ክለቦች ታውቀዋል። የቀጣይ ተጋጣሚዎች ድልድልም ይፋ ተደርጓል።
ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ የሚደረጉ አራቱም ጨዋታዎች ነገ እሁድ በመልካ ቆሌ ሜዳ እና በሼህ ሁሴን አላህሙዲ ስታዲየም ሲደረጉ :-
👉 ቁንዝላ ከ ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ
👉 ቆቦ ከ ደሴ ከነማ ቢ
👉 ሙጃ ከ ጎንጅ ደብረ ጥበብ እንዲሁም
👉 ጣና ክፍለ ከተማ ከ መካነ ኢየሱስ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
የውድድሩ አዘጋጅ ከቀጣይ ዓመት የአንደኛ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ቁጥር ጋር በተገናኘ ተጨማሪ ክለቦችን የማካተት ዕድል እንደሚኖር ገልጿል።
በአንዳንድ ጨዋታዎች ላይ የታዩ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እና ከጨዋታ ውጭ አጨዋወትን ተከትሎም ሥነ ሥርዓት ኮሚቴው የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
ዘጋቢ:- አማኑኤል ጸጋዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!