የጣና ሞገዶቹ የዘንድሮውን የኢትዮጵያን ፕሪምየር

37

ሊግ ውድድር በድል አጠናቀቁ።

ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጣና ሞገዶቹ ዛሬ ወላይታ ድቻን አንድ ለባዶ በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የብር ሜዳሊያ በመረከብ አጠናቅቀዋል።

በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው አደም አባስ በ47ኛው ደቂቃ ግብ በማስቆጠር ባሕርዳር ከተማ የሊጉን ፍጻሜ በድል እንዲቋጩት አድርጓል።

የጣና ሞገዶቹ አሠልጣኝ ደግአረግ ይግዛው ክለቡን በቀጣይ ልክ እንደ ሊጉ ሁሉ በአፍሪካ መድረክም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንሠራለን ብለዋል ከጨዋታው በኃላ።

በ60 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ባሕር ዳር ከተማ ከጨዋታው በኃላ የብር ሜዳሊያ ተረክቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአማራ ክልል በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ይሳተፋሉ” የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
Next article“ሌብነትና ብልሹ አሠራር የከተሞቻችን ዕድገት ፈተና ኾኗል” ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ