“በአማራ ክልል በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ይሳተፋሉ” የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

36

ባሕር ዳር: ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ክልላዊ የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ተጀምሯል።
የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እርዚቅ ኢሳ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአማራ ክልል እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት በተሠራው ሥራም የማኅበረሰቡ የመቀራረብ ባሕል እያደገ መምጣቱን ነው ያነሱት።

በ2014 ዓ.ም የክረምት ወራት በክልሉ 5 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሳተፍ ከ4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ ማዳን ተችሏል።
በ2015 ዓ.ም የክረምት ወራትም፦

👉 ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች በ13 የሥራ መስኮች ይሳተፋሉ። በዚህም ከ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ የሚሸፍን ሥራ ለመሥራት ታቅዷል።

👉 በክልሉ ለመትከል ከታቀደው 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ችግኝ 50 በመቶ የሚኾነው በወጣቶች የሚተከል ይኾናል።

👉 ከ3 ሺህ 400 በላይ አዲስ ቤቶች ይሠራሉ።

👉 ከ 7 ሺህ 500 በላይ ነባር ቤቶች የጥገና ሥራ
ይሠራል።

👉ከ250 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ይቀርባል።

👉ከ1 ሺህ 900 በላይ ትምህርት ቤቶች የማጠናከሪያ ትምህርት ይሰጣል።

የኢፌዴሪ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንሰትር ኤርጎጌ ተስፋየ (ዶ.ር) የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው መኾኑን አንስተዋል። ባለፉት ዓመታት ወጣቶች በመደራጀት ምርታማነትን ለማሳደግ እና ብሄራዊ ስሜትን ለማጎልበት የተለያዩ ሥራዎች ሲሠሩ ቆይተዋል። በ2015 ዓ.ም የክረምት ወራትም በ13 የሥራ መስኮች ከ20 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሳተፉ ነው ሚኒስትሯ የገለጹት።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአምስተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ አሥተዳደር ተካሂዷል።
Next articleየጣና ሞገዶቹ የዘንድሮውን የኢትዮጵያን ፕሪምየር