የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ አመራሮች በጅግጅጋ የተከሰተው የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ።

28

ባሕር ዳር: ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አያን አብዲን ጨምሮ ከሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጅግጅጋ በትናንትናው ዕለት ሌሊት ታይዋን ተብሎ በሚጠራው የገበያ ስፍራ የተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።

እሳት አደጋው ያደረሰውን ጉዳት የተመለከቱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ፣ በእሳት አደጋው ንብረታቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች የተሰማቸው ሀዘን ገልጸው፣ መንግሥት በሁሉም ነገር ለተጎጂዎቹ ድጋፍ እንደሚያደረግ ተናግረዋል።

በጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማዕከል ትናንት ሌሊት የተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተቋማትና ድርጅቶች ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደቀጠሉ ነው።
Next articleበጦርነቱ የተጎዳውን የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል መልሶ ለመገንባት የሚያገለግል የእርዳታ ማሰባሰቢያ ድረ ገጽ ማበልጸጉን አንበሳ ባንክ አስታወቀ።