ስለ ባለማተቧ ሕጻን ሳይንሳዊ ትርጓሜም ሆነ ማረጋገጫ ለመስጠት መቼገራቸውን የጤና ባለሙያው ተናገሩ።

315

ስለ ባለማተቧ ሕጻን ሳይንሳዊ ትርጓሜም ሆነ ማረጋገጫ ለመስጠት መቼገራቸውን የጤና ባለሙያው ተናገሩ።

ከሰሞኑ በዳንግላ ወረዳ ውፍጣ ዳጢ ቀበሌ የአንገት ማተብ አስራ ተወለደች ስለተባለችው ሕጻን በአካል ለማረጋገጥ ስፍራው ድረስ ያቀኑት ሐኪም ስለሁኔታው “ሳይንሳዊ ትርጓሜም ሆነ ማረጋገጫ የለም” ብለዋል፡፡

በዳንግላ ሆስፒታል የማኅፀንና ፅንስ ቀዶ ጥገና ሐኪም ያለው ፈለቀ ‹‹ምልክቱ አብሮ ተወልዷልም፤ አልተወለደምም ማለት አይቻልም፤ ሕጻኗ ከተወለደች ከአንድ ወር በላይ ሆኗታልና›› ብለዋል፡፡ ይህን ትክክለኛ ማረጋገጫ መስጠት የሚችሉት አዋላጅ ሐኪሞቹ ብቻ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን አዋላጅ ሐኪሞቹ በወቅቱ ላያስተውሉ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችልም ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል፡፡

በቦታው ተገኝተው ከተመለከቱ በኋላ ለአብመድ ሲናገሩም ‹‹ምልዕክቱ የተቋጠረ ነገር የለውም፤ ከእትብት ጋርም ምንም አይገናኝም›› ሲሉ ጉዳዩን አብራርተዋል፡፡ ክስተቱ ግን ተጨማሪ ምርምር እንደሚያስፈልገው ነው ሐኪሙ የተናገሩት፡፡ አሁን በተመለከቱት ነገር ተመሥርተው ድምዳሜ ለመድረስ ግን አስቸጋሪ እንደሆነ ነው ያስታወቁት።

አብመድ በቦታው ተገኝቶ ቤተሰቦችን ካነጋገረ በኋላ የባለሙያ ማብራሪያ እንደሚያቀርብ ቃል ገብቶ እንደነበር ይታወሳል።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሺባባው

Previous articleኬንያዊዋ ተመራማሪ ከወዳደቁ ፕላስቲኮች የቤት ግንባታ ቁሳቁስ እያመረቱ ነው፡፡
Next articleመንግሥት በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ቢያተኩር ችግሮች ሊቀንሱ እንደሚችሉ ወጣቶች ተናገሩ፡፡