
ባሕር ዳር: ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት የ2015 በጀት ዓመት የ11 ወር ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ የ11 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለቋሚ ኮሚቴው አቅርቧል።
የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የመንገድ ቢሮ ኀላፊው ሙሐመድ ያሲን እንዳሉት ቢሮው በበጀት ዓመቱ እየተሠሩ ከሚገኙት 541 ፕሮጀክቶች 500 የሚኾኑትን ለማጠናቀቅ ታቅዶ እንደነበር ተናግረዋል።
ከታቀደውም ባለፉት 11 ወራት 481 ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ መቻሉን ነው ቢሮ ኀላፊው በሪፖርታቸው ያመላከቱት።
በበጀት ዓመቱ 74 የመንገድ ግንባታ፣ 43 የድልድይ ግንባታ ፣ 369 የመንገድ ጥገና ሥራዎች መሠራታቸው ነው የተገለጸው።
በመንገድ ግንባታው ዘርፍ በኅብረተሰብ ተሳትፎ በምሳሌነት የሚጠቀስ ሥራ ተከናውኗል ብለዋል ቢሮ ኀላፊው በሪፖርታቸው።
ለመንገድ ጥገናና ጠረጋ ሥራው ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን በላይ ብር ከኅብረተሰቡ መሰብሰብ መቻሉን ነው የተናገሩት።
ዘጋቢ:- ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!