ባሕር ዳር: ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝሞ ቢሮ አዘጋጅነት “ባሕላችን ለሰላማችንና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ ከሐምሌ 1 እስከ 2/2015 ዓ.ም የሚቆይ የባሕል እና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል በባሕርዳር ከተማ ተጀምሯል።
በፌስቲቫሉ ላይ ከክልሉ የተለያዩ ዞኖች እና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ የባሕል እና ኪነ ጥበብ ቡድን አባላት ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ ጣሂር ሙሐመድ “የባሕል ፌስቲቫሉ የተሳሳቱ ትርክቶችን አርሞ የሕዝባችንን እውነቶች ለማሳየት ኹነኛ መንገድ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ፌስቲቫሉንም ሪቫን ቆርጠው አስጀምረዋል። በሙሉዓለም የአማራ ባሕል ማዕከል ውስጥ የተለያዩ የባሕል አልባሳት፣ ቁሳቁስ እና ባሕላዊ ምግቦችም ለዕይታ ቀርበዋል።
ከየዞኑ የመጡ የባሕል ቡድን አባላት የያዟቸውን ጥበባዊ ሥራዎች አቅርበው የየአካባቢያቸውን ማኅበረሰብ ባሕል እና እሴት የሚያስተዋውቁ ይኾናል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!