
በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ፣ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በ13 የበጎ ፈቃድ የሥራ ዘርፎች የሚካሄደው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤትን በማደስ ሥራ ተጀምሯል።
በዛሬው መርሐ-ግብር ከቤት እድሳት ባሻገር የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ እና የማጠናከሪያ ትምህርት የማስጀመር ተግባራት እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!