
ደሴ: ሰኔ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ተማሪዎቹ ላለፉት 3 ወራት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል። ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ፈተና ሂደት የተማሪዎችን አቅም ለማጎልበት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ታምሬ ዘውዴ (ዶ.ር) ለአሚኮ ተናግረዋል።
በሌላ ዜና በዛሬው እለት ከተለያዩ የግልና የመንግስት የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን በመካነ ሰላምና ቱሉ አውሊያ ግቢ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) መፈተን መጀመሩንም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ጀማል ይማም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!