
ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ሞኒክ ሳንዛባጋንዋ (ዶ.ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ምክትል ሊቀመንበሯ አሁን ላይ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እየተካሄደ ስላለው ማሻሻያ በተመለከተ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገላጸ አድርገዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠውላቸዋል፡፡
ኮሚሽኑ ለሚያካሂደው የማሻሻያ ሥራ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን መግለጻቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!