
ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ ከሐምሌ ስምንት ጀምሮ ክፍት እንደሚኾን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ወደ ከፍተኛ ሊግ ከወረዱት ከአርባምንጭ ከተማ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ተጨዋቾች የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል። አዲስ አዳጊዎቹ ሻሸመኔ ከተማ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተጫዋች ዝውውር ጊዜውን ይጠቀሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
መስከረም 25/2016 ድረስ የሚቆየው ዝውውር ጊዜ የተጫዋቾች ዝውውር ሕጋዊነት የሚፀድቀው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ተገኝቶ በመፈራረም ብቻ መኾኑን አሳስቧል።
በክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በሌላ አካል በኩል የሚደረግ ስምምነት ተቀባይነት የሌለው መኾኑን ጨምሮ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!