
አዲስ አበባ: ሰኔ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በጤና ሚኒስቴር እየተዋወቀ ያለው ድጅታል የክፍያ ሥርዓት ለአገልግሎት ምቹ፣ ቀላል እና የጤናውን ዘርፍ ተደራሽነት ማረጋገጥ የሚያስችል እንደኾነ ተገልጿል፡፡
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ.ር) እንዳሉት በጤናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ የአሠራር ችግሮችን ለመቅረፍ ብሎም የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እና አገልግሎት ሰጪዎችን ለማስተሳሰር ዲጂታል የክፍያ ሥርዓትን መገንባት አስፈላጊ ነው።
ዶክተር ሊያ ዲጅታል የክፍያ ሥርዓት አገልግሎትን በማቀላጠፍና ሰፊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን በማረጋገጥ የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱ እንዲዘምን ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም ገልጸዋል።
ይህ በጤናው ዘርፍ ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት የመገንባት ሂደትም በሚቀጥለው አስር ዓመት ሀገሪቱ ለማሳካት ያቀደችውን ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን የሚያደርግ ነውም ተብሏል።
አሁን ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም የፓናል ውይይት እየተካሄደም ነው፡፡
ዘጋቢ፡- ቤተልሔም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!