“ምቹና አስተማማኝ ሥራ ለአፍሪካ ብልፅግና ” በሚል መሪ ሃሳብ የመጀመሪያው የአፍሪካ የሥራ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

45

አዲስ አበባ: ሰኔ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ኀብረት የኢኮኖሚ ልማት፣ ንግድ፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽነር አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ የጉባዔው ዋና ዓላማ በዲጂታል እና ፋይናንስ የታገዘ የሥራ ፈጠራን በማበረታታት እና በተግባር ላይ በማዋል አፍሪካን በሥራ ፈጠራ ቀዳሚ ማድረግ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው ጉባዔ ወጣቶች፣ አምራቾች እና ሥራ ፈጣሪዎች ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ እንደሚኾንም ተናግረዋል። በዚህ የመጀመሪያ በኾነዉ የአፍሪካ የሥራ ጉባኤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የቀድሞ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ፣ የአፍሪካ ኀብረት የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በጉባኤው የተለያዩ አምራች ድርጅቶች እና ግለሰቦች ምርቶቻቸውን ለእይታ አቅርበዋል። ጉባኤው ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአማራ ሕዝብ ጥያቄ የሚመለሰው ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር ነው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
Next article“የግል ትምህርት ቤቶች ከትርፍ ባሻገር ሚናቸውን በልኩ መወጣት አለባቸው” ዶክተር ማተብ ታፈረ