
ደባርቅ: ሰኔ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በወረዳው በ5 የችግኝ ማዘጋጃ ጣቢያዎች ለማዘጋጀት ከታቀደው 538 ሺህ ችግኝ ውስጥ 528 ሺህ የሚኾነው ተዘጋጅቷል።
ከተዘጋጁት ችግኞች 23 ሺህ የሚኾኑት የፍራፍሬ ችግኞች መኾናቸውን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ስለሽ በርሔ ለአሚኮ ገልጸዋል።
የችግኝ ዝግጅቱ በሕዳር/2015 ዓ.ም የተጀመረ ሲኾን ለ348 ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉንም ኀላፊው አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡- ተስፋየ አይጠገብ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!