ወደ ጥሎ ማለፍ የገቡ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል!!

54

ወልድያ: ሰኔ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ15ተኛው የአማራ ክልል እግር ኳስ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ላለፉት 10 ቀናት ሲካሄዱ ቆይቷል። በ9 ምድቦች ተከፍለው ጠንካራ ፉክክር ሲያደርጉ ከነበሩ ክለቦች መካከልም ቀጣዩን ዙር የተቀላቀሉ እና ከምድባቸው ማለፍ ያልቻሉ ክለቦች ተለይተዋል።

የምድብ ጨዋታዎቹ መጠናቀቃቸውን ተከትሎ የውድድሩ አዘጋጅና የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚ ክለቦችን ድልድል ይፋ አድርጓል። የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎቹም ከዛሬ ጀምሮ እየተካሄዱ ነው።

በተያያዘ ዜና ከእስካሁኑ የውድድሩ አካሄድ ጋር በተገናኘ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎች ተላልፈዋል። የውድድሩ አዘጋጅና ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ የቀረቡለትን አቤቱታዎች ተከትሎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ደንብና መመሪያ መሠረት የቅጣት ውሳኔዎቹን አስተላልፏል።

በዚህም የማቻከል ቡድን መሪ እና የጃማ ደጎሎ እግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሚመራቸው ውድድሮች ለአንድ ዓመት እንዲታገዱ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በተጨማሪም የአማኑኤል ከነማ ፣ አዘዞ ድማዛ ፣ ጉቤ ወልዲያ ፣ አልብኮ ፣ ምንጃር እና ሸዋ በር ጋራዥ አንዳንድ ተጫዋቾች ከስፖርት አድራጎት ውጭ በመጫወትና ስፖርታዊ ጨዋነትን በማጓደል ለፈጸሙት ድርጊት በውድድሩ ደንብ መሠረት እንዲቀጡ ተደርጓል።

ዘጋቢ:- አማኑኤል ጸጋዬ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ግብርን በታማኝነት አለመክፈል ሀገርን መስረቅ ነው” የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ
Next article“ኢትዮጵያ በየደረጃው ያጋጠሟትን ፈተናዎች ተሻግራ ብሔራዊ ጥቅሟን ማስጠበቅ ችላለች” አቶ ደመቀ መኮንን