ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የሕዳሴ ግድብ የራሷን በማያጓድል፣ የሌሎችን በማያሳጣ መልኩ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ፡፡

51

ባሕር ዳር: ሰኔ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የራሷን በማያጓድል፣ የሌሎችን በማያሳጣ መልኩ መኾኑንም አስታውቀዋል፡፡

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዳሴ ግድብ በከፍተኛ የአየር ጸባይ ተቋቁመው እየሠሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን ምሥጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ “የሱዳን እና ግብጽ ወንድሞቻችንና ጎረቤቶቻችንን ልንነጥላቸው የማንችል ሕዝቦች ናቸው፣ እነሱን ታሳቢ ያደረገ ሥራ እየሠራን ነው” ብለዋል፡፡

የእኛን በማያጓድል፣ የእነሱንም በማያሳጣ መልኩ እየሠራን ነውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ የኢትዮጵያ ፍላጎት የመልማት ብቻ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ ወደፊት የሚኖረው ሥራ ሌሎች ፕሮጄክቶችን እንዴት እንሥራ የሚለው ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሀገራቱ ጋር ለመወያየት እና ለመነጋገር ኢትዮጵያ ዝግጁ መኾኗንም አስታውቀዋል፡፡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሙሌቱም ሌሎችን በማይጎዳ መልኩ ይከናወናል ነው ያሉት፡፡ ዘንድሮ የተሻለ ዝናብ መገኘቱም ለሙሌቱ መልካም አጋጣሚ ሊኾን እንደሚችል ነው ያነሱት፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሥራ አጥነትን መቀነስ ሰላምን ያመጣል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ሕገ-ወጥ ንግድ አሁንም ድረስ ሀገራዊ ፈተና ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)