የደቡብ ወሎ ዞን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደምብና ፕሮግራም ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡

369

የደቡብ ወሎ ዞን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደምብና ፕሮግራም ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡

ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ800 በላይ የደቡብ ወሎ ዞን በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአዲሱ የብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብና በፓርቲው ፕሮግራሞች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የውይይቱ ዓላማም በአዲሱ ፕሮግራም ዙሪያ ለዞንና ወረዳ የሥራ ኃላፊዎች ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ሕዝቡ ወርደው የፕሮግራም ግልፅነት ለመፍጠር እንዲችሉ ማስቻልን መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ ሙሐመድ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡

ውይይቱ ዛሬና ነገ የሚደረግ ሲሆን በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፦ አሊ ይመር -ከደሴ

Previous articleዕርቀ ሠላሙ ውጤታማ እንዲሆን ባለፉ ታሪኮች ላይ መግባባት እንደሚገባ የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡
Next articleበኩር ታህሳስ 6/2012 ዓ/ም ዕትም