
ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጂቡቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ጋር በመሆን በአይ ሲቲ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
የጂቡቲ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታ ሲራጅ ዑመር የተመራው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን በአይ ሲቲ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
በዚህ ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንደተናገሩት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ ጉብኝት የአረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲን የበለጠ የሚያጠናክር ነው።
የመጪው ትውልድ የልማት መሰረት የሆነውን ችግኝ መትከል የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በአረንጓዴ ልማት ለማስተሳሰር የበለጠ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።
ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአረንጓዴ አሻራ ላደረገው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።
የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር ዓላማው በማድረግ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ይታወቃል።
የጂቡቲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ትናንት ኢትዮጵያ መግባቱ ይታወሳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!