
ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) የፌደራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ያዳምጣል፡፡
ምክር ቤቱ በውሎው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን እንደሚያጸድቅም የጠበቃል።
መረጃው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!