
ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል።
የድጋፍ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ተፈራርመዋል።
ኅብረቱ ድጋፉን ያደረገው ኮሚሽኑ እያከናወነ ያለው ሀገራዊ ምክክር በውጤት እንዲጠናቀቅ በማለም ነው።
በስምምነቱ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!