የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሥራና ስልጠና መምሪያ ከ25 ሺ በላይ ለሚኾኑ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ ።

47

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሥራና ስልጠና መምሪያ በ2015 በጀት ዓመት ለ28 ሺ 941 ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር አቅዶ 25 ሺ 546 ወጣቶችን የሥራ እድል መፍጠሩን ገልጿል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ሥራና ስልጠና መምሪያ ኀላፊ ወ/ሮ ባይሴ ሚጀና እንደገለፁት የባለፈውን ዓመት አፈፃፀም መነሻ በማድረግ ለ2015 ምን ያህል የሥራ እድል እንፍጠር ብለን በገጠር በከተማ ያሉ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች፣ ከስደት ተመላሾች ለሁሉም በየደረጃው ያሉ ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን በመመዝገብ የግንዛቤ በመፍጠር በግብርና፣ በኮንስትራክሽን፣ በእርባታ እና መሰል ዘርፎች በማደራጀት የተዘዋዋሪ ብድር 25 ሚሊየን ብር በማመቻቸት ወጣቶችን ወደ ሥራ ማሰማራት መቻሉን ገልፀዋል ።

እንደ መምሪያ ኀላፊዋ ገለፃ የወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 14 ፐርሰንት ለውጥ ያሳየ 11246 ብልጫ ማሳየቱን ገልፀዋል ለዚህ ውጤት አፈፃፀም መሳካት የዞኑ ግብረሃይል በጥምረት በመሆን ለስራው ትልቅ ትኩረት በመስጠት በጋራ በመረባረብ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

ወጣቶቹ በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍም ተጠቃሚነታቸው የጎላ ነው ብለዋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን መረጃ እንደሚያሳየው፤ 2016 በጀት አመት ለ34ሺ ስራ አጥ ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር አቅደው እየሠሩ መሆኑን ኀላፊዋ ተናግረዋል ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበበጀት ዓመቱ 42 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ከ4 መቶ በላይ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስታወቀ።
Next articleየአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።