በበጀት ዓመቱ 42 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ከ4 መቶ በላይ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስታወቀ።

45

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን በ2015 በጀት ዓመት 42 ነጥብ 8 ቢሊዮን ካፒታል ላስመዘገቡ ለ4 መቶ 64 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱት ድርጅቶች ለ1 መቶ 26 ሺህ 7 መቶ 20 ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥሩ የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና የኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን መሪ ወይዘሮ ትእግሥት ይገዙ ገልጸዋል።

ወይዘሮ ትእግስት በበጀት ዓመቱ 2 መቶ 64 በተለያየ የኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚሰማሩ ፕሮጀክቶች ተገምግመው ማለፋቸውንና ተገምግመው ማለፋቸውን ገልጸዋል።

ተገምግመው ካለፉት 99 ፕሮጀክቶች ውስጥ 2 ሺህ 9 መቶ 38 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ማስተላለፍ ተችሏል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ 136 ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ መግባታቸውን እና 20 አምራች ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው መጠናቀቁን ወይዘሮ ትእግስት ተናግረዋል።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያሳየው፤ ቡድን መሪዋ አክለውም 31 ፕሮጀክቶች ወደ ምርት ማምረት እና አገልግሎት መስጠት ተሸጋግረዋል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በክልሉ ከ32 በላይ የቱሪስት መዳረሻ ቅርሶች ጥገና ላይ ናቸው” ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ
Next articleየኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሥራና ስልጠና መምሪያ ከ25 ሺ በላይ ለሚኾኑ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ ።