በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዛሬ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ።

41

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በሚካሄዱ ሁለቱ ጨዋታዎች ይጀመራል።

በመርሐ-ግብሩ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በደረጃ ሰንጠረዡ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ 42 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው በቅደም ተከተል አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ፋሲል ከነማ በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ፤ በሁለቱ ተሸንፎ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ አቻ ወጥቷል።

ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች በሁለቱ አሸንፎ በአንዱ ተሸንፎ በሁለቱ ነጥብ ተጋርቷል።

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ነው።

ሌላኛው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ያገናኛል።

በደረጃ ሰንጠረዡ ሲዳማ ቡና በ38 ነጥብ 10ኛ ሲሆን አስቀድሞ ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ12 ነጥብ የመጨረሻውን 16ኛ ደረጃ ይዟል።

ሲዳማ ቡና በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ በአንዱ ተሸንፏል፤ በሁለቱ ደግሞ አቻ ወጥቷል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በበኩሉ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች በአራቱ ተሸንፎ አንድ ጊዜ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያ ዙር ባደረጉት ጨዋታ ሲዳማ ቡና 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐምሌ 1/2015 ይጠናቀቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ከስጋት ይልቅ የትብብርና የመልማት ጥያቄን እንዲመልሱ እየሠራች ነው።
Next article“በክልሉ ከ32 በላይ የቱሪስት መዳረሻ ቅርሶች ጥገና ላይ ናቸው” ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ