
ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
ከትናንት የቀጠለው ጉባኤው ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ቀድሞ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ናቸው። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛው የፓርላማ ዘመን በ1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔ አስፈጽሞ ሪፖርት እንዲያደርግ መታዘዙን የሚታወስ ነው። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔውን በማስፈጸም ያዘጋጀው ሪፖርት እንደኾነ ገልጸዋል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚደረግ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!