የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

40

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርት ያዳምጣል፡፡

ሕዝበ ውሳኔውን አስመልክቶም በቋሚ ኮሚቴው የሚቀርበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ሌሎች መደበኛ የመወያያ አጀንዳዎችን በማጽደቅ እየተወያየ ነው ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱ ያጸደቃቸውን አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው ይጠበቃል መባሉን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያን የምርጫ ሥርዓት ለማጠናከር የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ።
Next article“ለ15ኛ ጊዜ ለሚዘጋጀው የአማራ ክልል የባሕልና ኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቅቋል።” የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ ጣሂር ሙሐመድ