“የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

98

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞን ያንጋቶም ወረዳ ዐሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው “ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞን ያንጋቶም ወረዳ ዐሻራችንን አሳርፈናል። “ብለዋል፡፡

“በእንደዚህ ዓይነት አካባቢ የምናደርገው ጥረት የድርቅን ሥጋት ለመከላከል ያለመ ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

እነዚህን ተግባራት በማስቀጠል ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል ፍሬያማ ውጤት ማግኘት እንችላለንም ነው ያሉት፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰላም ከሌለ በጀቱ ልማትን ሊያሳካ አይችልም” የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት
Next article“የሥርዓተ ምግብ ችግር አኹንም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ሀገራዊ አጀንዳ ነው” የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ.ር)