
ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመደበኛ ጉባዔው በ2016 ዓ.ም ሪቂቅ በጀት ላይ እየተወያየ ይገኛል፡፡
የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ውይይት የተዘጋጁ እና ከሕዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን እያቀረበ ነው።
በዚህም መሠረት፦
➡ለባለ በጀት የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች የተደለደለው በጀት የተቋማትን የመፈጸም አቅም፣ የሥራ ስፋት፣ የተቋሙን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ ፋይዳ እና የኦዲት ግኝትን ምን ያክል ታሳቢ ያደረገ ነው? ምን ያክል ወጪ ቆጣቢና ውጤትን መሠረት ያደረገ አመዳደብ ነው?
➡በጀት ተይዞላቸው የነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ሽግሽግ በሚል ምክንያት የተያዘላቸው በጀት ተነስቶ ሳይጀመሩ ቀርተዋል፡፡ ተጀምረው የተቋረጡም አሉ በ2016 በጀት ዓመት እነዚህ ፕሮጀክቶች ታሳቢ ያደረገ ነው ወይ?
➡የዋጋ ግሽበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቶ አሁን ላይ ተንከባላይ የዋጋ ግሽበት 33 ነጥብ 37 በመቶ ደርሷል፡፡ ይህም ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የከተማ ነዋሪና የመንግሥት ሠራተኛውን በእጅጉ እየፈተነ መጥቷል፡፡ በ2016 በጀት ዓመት የዋጋ ግሽበቱ የበለጠ እንዳይጎዳቸው ምን ታስቧል? የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ እና ሌሎች አማራጮችን ለመውሰድ ምን ታስቧል?
➡ከጠቅላላ ሀገራዊ በጀት ለካፒታል ወጪ የተመደው በጀት ቅናሽ አሳይቷል በዚህ ላይ መብራሪያ ቢሰጥበት? የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።
ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!