ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አርባምንጭ ከተማ ገቡ።

76

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡

አርባምንጭ ከተማ ሲገቡም በአካባቢው ነዋሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ምዕራፍ ሁለት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 ሻምፒዮን ኾነ
Next articleየ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ የምክክር መድረክ ተካሄደ።