
ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረው የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መኾኑን አረጋግጧል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የኾነው ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 በኾነ ውጤት በማሸነፍ ነው፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሀድያ ሆሳዕና ያገናኘው የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮን የኾነባቸውን ግቦች ቸርነት ጉግሳ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ አስቆጥረዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!