
ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጽያ ኘሪሚየር ሊግ ጨዋታ የጣና ሞገዶቹ ሀዋሳ ከተማን አሸንፈዋል።
በፕርሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ የኾነው እና በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው ባሕር ዳር ከተማ በአብስራ ተስፋዬ ብቸኛ ግብ ነው ተጋጣሚውን የረታው።
የአፍሪካ መድረክ ተሳትፎቸውን ቀድመው ያረጋገጡት የጣና ሞገዶቹ በ29 ጨዋታዎች 57 ነጥብ በመሰብሰብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በ6 ነጥብ ዝቅ ብለው በ2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አንድ ነጥብ እየቀረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮን መኾኑን ዛሬ አረጋግጧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!