
ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወናጎ ከተማ ሲገቡ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወናጎ ቆይታቸው የሁለተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አካል የሆነ ችግኝ ተከላ እንደሚያከናውኑ ይጠበቃል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!