
ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በየትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ የተማራችሁ ሁሉ ትናንት የተማራችሁባቸው ትምህርት ቤቶች ዛሬ የናንተን ድጋፍ ይሻሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁሉም ዜጎችና ተቋማት ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ “ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄንም አስጀምረዋል።
ያለትምህርት መስፋፋት በመጪው ዓለም ተወዳዳሪ መኾን ስለማንችል ስለትምህርት ዛሬ የሚጠበቅብንን ልንወጣ ይገባልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!