
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 26/2012ዓ.ም (አብመድ) በምሥረታ ሂደት ላይ የሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና መሠረታዊ እሳቤ ላይ እየተወያዩ የሚገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ሚንስትሮች፣ ሚንስትር ዴኤታዎች እና ሌሎችም ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው፡፡
በውይይቱ ኢሕአዴግ የነበሩት መልካም ልምዶችና ክፍተቶች እየተነሱ የሚታረሙበት አግባብ ተመላክቷል፡፡ የብልጽግና ፓርቲ እውነተኛ የፌዴራሊዝም ሥርዓት እውን የሚሆንበት እንደሆነም በውይይቱ ተነስቷል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ በፕሮግራሙ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ዘላቂ መንግሥታዊ መዋቅርና ተቋማት መገንባት፣ የብሔር ማንነትና ሀገራዊ አንድነት ሚዛን የጠበቀ ማድረግ፣ አንድ ጠንካራ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መፍጠር ዓላማዎቹ እንደሆኑ ተነስቷል፡፡
የውጭ ጉዳይ እና የፖለቲካል ኢኮኖሚ ጉዳዮች በብልጽግና ፓርቲ ዕይታም ውይይት እየተደረገባቸው ነው፡፡
ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ -ከአዲስ አበባ