
ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 27/2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ለመስጠት የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁ ተገልጿል።
ለፈተናው አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ወደ ትምህርት ቤቶች የማጓጓዝ ሥራው ያለምንም ችግር የተጠናቀቀ ሲሆን በአስፈታኝ ትምህርት ቤቶች ለፈተና አስፈፃሚዎች እና ተፈታኝ ተማሪዎች ኦሬንቴሽን የመስጠት ሥራው ከሰኔ 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ በማኅበራዊ የትስስር ገጹ እንደገለጸው በአማራ ክልል 347,966 ተማሪዎች በ5752 ትምህርት ቤቶች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በሁሉም አካባቢዎች የትምህርት ማኅበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ ይገኛሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!