
ባሕር ዳር: ሰኔ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ዓለምብርሃን ይግዛው በ40ኛው እንዲሁም ጋናዊው አጥቂ ኦሴይ ማውሊ በ50ኛ ደቂቃ ለፋሲል ከነማ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ አብዱራህማን ሙባረክ በ87ኛው ደቂቃ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ42 ነጥብ ከነበረበት 8ኛ ደረጃ ወደ 4ኛ ከፍ ብሏል።
በአንጻሩ ከፕሪሚየር ሊጉ አስቀድሞ መውረዱን ያረጋገጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ12 ነጥብ የመጨረሻውን 16ኛ ደረጃን ይዟል።
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!