“የጥናትና ምርምር ተግባራት ለምናከናውነው ተቋማዊ ተግባርና አላማ አጋዥ ይሆናሉ።” አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

51

አዲስ አበባ: ሰኔ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሦስተኛውን የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ክቡር ታገሰ ጫፎ የጥናትና ምርምር ተግባራት ለምናከናውናቸው ተቋማዎ ተግባርና አላማ አጋዥ ይሆናሉ ብለዋል።

የዚህ ዓመታዊ ኮንፈረንስ አላማም ምክር ቤቱ በሀገራዊና ተቋማዊ ተግባር ውስጥ ተጨባጭና ግብ ተኮር አሠራሮች ላይ አተኩሮ እንዲሠራ አቅም ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል አፈጉባዔው።

እስካሁንም ከ60 በላይ የጥናት ሥራዎች ቀርበው

13 መስፈርቱን አሟልተው ተመርጠዋል ብለዋል።

የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ምክር ቤቱ አቅም ያለው ሕግ አውጭና ተቆጣጣሪ የሰው ኀይል እንዲኖረው ለምርምር ዋጋ ሰጥቶ ለአጥኚዎች መስጠቱ ያስመሰግነዋል ብለዋል። የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች በምክር ቤት በውይይት ክርክርና ሙግት አብላጫ መፍትሔ ወስደው ወደ ሕዝብ ይመጣሉ ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ይህን መሰል ጥናት ተኮር ተግባራት ደግሞ ውጤታቸው በሥርዓትና በዕውቀት የሚመራ እንዲኾን ያደርጋል ብለዋል።

ይህ የፓርላማ ጥናትና ምርምር መደረጉም

የዕውቀት ሽግግር፣ የሳይንሳዊ ዕውቀት ግብይት፣

በቋሚ ኮሚቴና መላ አባላቱ መካከል የውስጥ አቅም ማጎልበትና ተመራማሪዎች በምክር ቤት ተግባራት እንዲያውቁና እንዲሳተፉ ማድረግ በአላማነት ከተያዙት ናቸው ተብሏል።

ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከተሜነት መሰረተ ልማት በተሟላበት እና ጽዱ በኾነ ከተማ ውስጥ መኖር ነው” የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ አገኘሁ ካሳ
Next articleአጼዎቹ ደረጃቸውን ወደ አራተኛ ከፍ ያደረጉበትን ድል አስመዘገቡ።