ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር የ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት መድኃኒት ለደሴ ከተማ፣ ለደቡብ እና ለሰሜን ወሎ ዞኖች ድጋፍ አደረገ።

64

ባሕር ዳር: ሰኔ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የምስራቅ አማራ ኢመርጀንሲ አስተባባሪ አቶ እንግዳ አሻ በጦርነት ጉዳት የደረሠባቸውን አካባቢዎች በጤናው ዘርፍ ለመደገፍና ለማቋቋም በቀጣናው በዋናነት በ5 ዞኖችና ከተማ አስተዳደር ላይ በሚገኙ 24 ወረዳዎች ላይ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።

በዛሬው እለት ድጋፍ ያደረገውም በቀጣናው በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ከ430 ሺህ በላይ የህጻናትና እናቶችን ሞት የሚቀንስ የመድኃኒት ድጋፍ እንዳደረጉ ገልጸዋል።
በቀጣይም ድጋፉን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

የደሴ ከተማ ጤና መምሪያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል ባለሙያ አቶ ብርሀኑ ፈንታው፤ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር ከአሁን በፊት ለአንድ ዓመት ያህል በጦርነት የወደሙና ለተጉዱ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች ድጋፍ አድርጓል ።

አሁን ደግሞ ለከተማችን ማኅበረሰብ ከ1ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሜዲካል መድኃኒቶችን በመስጠት በተለይ ለእናቶችና ህፃና የሚኾን መድኃኒቶችን በሰፊው ስላቀረቡልን ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፈለቁ መኮንን በዞናችን ከጦርነቱ ተያይዞ የጤና ተቋማቶቻችን በርካታ ውድመት የደረሰበት አካባቢ ነው ብለዋል።

የዞናችን ማኅበረሰብም በጦርነቱ የተፈናቀሉ፣ የተቸገሩና የተጎዱ ወገኖች የሚገኝበት አካባቢ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ ህክምና ላይ ከፍተኛ ችግር እንደገጠማቸው ገልጸዋል።

አሁን ላይ ወርድ ቪዥን ያደረገልን ድጋፈ በርካታ ህጻናትና እናቶች የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ አድርጓልናል ብለዋል። መረጃው የደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሽጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የፅኑ ሕክምና መሣሪያወች ድጋፍ ተደረገለት።
Next article“ኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ስኬቶችንም አስመዝግባለች” ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)