
ባሕር ዳር: ሰኔ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሽጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሕክምና መሣሪያች ድጋፍ ተደርጎለታል።
የሕክምና መሣሪያዎች ሆስፒታሉ የአዋቂዎች ፅኑ ሕክምና አገልግሎት ክፍልን ለማስጀመር የሚያግዙ ናቸው። ለፅኑ ሕክምና ወደ ሌላ ተቋማት ሪፈር የሚባሉ ሕመምተኞችን በተወሰነ መልኩ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ሆስፒታሉ ከሚያገለግለው የሕዝብ ቁጥር አንፃር አሁን ላይ በድጋፍ መልኩ የተገኘው የአዋቂዎች የፅኑ ሕክምና መሣሪያወች በቂ ባለመሆናቸው እና በፅኑ ከታመሙት ታካሚዎች መካከል ሞት፣ የሕመምን ሪፈርን እና እንግልትን ለመቀነስ ከጤና ቢሮ እና ከኅብረተሰቡ ቀጣይነት ያለው የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ሆስፒታሉ ጠይቋል።
ሞኒተሪንግ ማሽን ፣ መካኒካል ቬንትሌተር፣ ሰክሽን ማሽን
፣ ፖርቴብል አልትራሳውንድ ፣ የታካሚ አልጋዎች እና ዊልቸር የሕክምና መሣሪያዎች ለሆስፒታሉ ድጋፍ መደረጋቸውን ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!