
ደብረታቦር: ሰኔ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ጉና በጌምድር ወረዳ ክምር ድንጋይ ከተማ ውስጥ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየተመረቁ ነው።
ከተማዋ በጦርነት ከፍተኛ ውድመት ቢደርስባትም የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በመልሶ ግንባታ ላይ ትገኛለች። በከተማዋ በርካታ አዳዲስ የከተማ መሰረተ ልማት ግንባታዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ግንባታቸው የተጠናቀቁ የልማት ሥራዎች ዛሬ ይመረቃሉ። የውስጥ ለውስጥ የመንገድ፣ የመብራት፣ የቁም እንስሳት የግብይት ቦታ፣ የውኃ ማፋሰሻ ቦይ፣ የጌጠኛ ድንጋይ ማንጠፍ እና የጠጠር መንገድ ግንባታዎች እንደሚመረቁ ተገልጿል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!