
ባሕር ዳር: ሰኔ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በትምህርት አቅርቦት ውስጥ አካታችነትን ለማጎልበት በምታደርገው ጥረት የሥርዓተ ጾታ ክፍተቱ እንዲዘጋና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን እንዲያገኙ የሚቻለው ሁሉ እየተደረገ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በተጨማሪም ለአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች መሠረተ ልማት እና የትምህርት አገልግሎቶችን ማስፋፋት፤ መደበኛ ያልሆነ ትምህርት እና የሥልጠና መርሐ ግብሮችን ለዐዋቂዎች መስጠት እና የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ከሚሠሩ ዋና ዋና ሥራዎች መኾናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳታውቀዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
