ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በጦርነቱ ለተጎዱ በአማራ እና አፋር ክልል ለሚገኙ የህክምና ተቋማት ድጋፍ አደረገ።

53

ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በጦርነቱ ለተጎዱ በአማራ እና አፋር ክልል ለሚገኙ የህክምና ተቋማት 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ.ር) ተረክበዋል።

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ያደረገዉ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በጦርነቱ የወደሙ የህክምና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል እንደኾነም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በአማራ እና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ለተጎዱ 12 ሆስፒታሎች እና 10 የጤና ጣቢያዎች አገልግሎት የሚዉል የህክምና ቁሳቁስ ነው ድጋፍ ያደረገዉ።

ድጋፉ የቀዶ ጥገና መሳሪያዎች፣ የጽኑ ህሙማን ማከሚያ ማሽኖች፣ የማዋለጃ የህክምና መመርመሪያ መሳሪያዎች፣ የላብራቶሪ እቃዎችና የአስተኝቶ ማከሚያ መሽኖችን ያካተተ ነዉ።

የሰዎች ለሰዎች የኢትዮጵያ ተጠሪ ይልማ ታየ ይህ ድጋፍ የወደሙ ተቋማትን ለማቋቋም የሚያስችል ነዉ ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleእስከ ቂያማ የምትዘልቀው የዘምዘም ውኃ
Next articleየአባትና ልጅ ለፈጣሪ ፍጹም የመታዘዝ የመሥዋዕትነት ፍሬ